Preview — VidLingo is opening soon. Things may still change.

VidLingo

← All picture books

የማር ቆራጩ መሪ በቀል

EasyAmharic · Read aloud
Picture for page 1 of የማር ቆራጩ መሪ በቀል

ይህ የማር ቆራጩ መሪ የንጌዴና ግንጊሌ የተባለ ገብጋባ ወጣት ታሪክ ነው። አንድ ቀን ግንጊሌ አደን ላይ ሳለ የንጌዴን ጥሪ ሰማ። ግንጊሌ ማርን አስቦ ጎመዠ። ከራሱ በላይ ባሉት የዛፍ ቅርንጫፎች ወፉን እስኪያየው ድረስ እየፈለገ ቆም ብሎ በጥንቃቄ አደመጠ። ‹‹ችክ፣ ችክ፣ ችክ›› በማለት ወደ ቀጣዮቹ ዛፎች እየበረረ ትንሹ ወፍ ጮኸ። ግንጊሌ መከተሉን እርግጠኛ ለመሆን ቆም እያለ እያየ ‹‹ችክ፣ ችክ፣ ችክ›› እያለ ተጣራ።

Page 1 of 11

Credits